በዚህ የበጋ ወቅት ላይ የማህበረሰብ የሙቀት መከታተያ መጠቆሚያ (heat mapping) ፕሮጀክት ላይ ይሳተፉ!

April 20, 2022
  |   1 Comment

English | Amharic / አማርኛ | Spanish / Español

በሞንትጎመሪ ውስጥ ያለው የሙቀጥ መጠን እየተሰማዎት ነው? በዚህ የበጋ ወቅት ላይ የማህበረሰብ የሙቀት መከታተያ መጠቆሚያ (heat mapping) ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ ይሁኑ!

በዚህ የበጋ ወቅት ላይ፣ የሙቀት መከታተያ መጠቆሚያዎችን ለማዘጋጀት እና በአካባቢያችን ላይ የሚገኘውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን ላይ የፈጠራ እና የቅንጅት መፍትሔዎችን ለማበጀት የሞንትጎመሪ ካውንቲ በአካባቢው የሚገኙ ድርጅቶች እና የበጎፈቃድ ተሳታፊዎችን በጋራ የሚያጣምር የማህበረሰብ የሙቀት መከታተያ መጠቆሚያ ፕሮጀክት እያከናወነ ነው። የሙቀት መዛባትን ለመከታተል ሞንትጎምሪ ካውንቲ ከብሔራዊ የውቅያኖስ እና የአየር አስተዳደር [National Oceanic and Atmospheric Administration] (NOAA) እና ከማህበረሰብ ሳይንቲስትቶች ጋር በጋራ ከሚሰሩት በአለም ውስጥ ከሚገኙት 16 ግዛቶች ውስጥ አንደኛው ይሆናል።

የከተማ የሙቀት ደሴቶች [Urban Heat Islands] ከፍተኛ ሙቀትን ከሚያባብሱ ሕንፃዎች፣ መተላለፊያ መንገዶች፣ እና ሌሎች የከተማ ክፍለ አካላት የተነሳ በአቅራቢያው ከሚገኙ መኖሪያ ስፍራዎች ጋር ሲነፃጸር ከ 20 ዲግሪ በላይ የሚደርስ የሙቀት መጠን ያላቸው ቦታዎች ናቸው።

እጅግ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከሌሎች የአየርንብረት ሁኔታዎች ይልቅ ብዙ አሜሪካውያንን ይገድላል፣ ነገር ግን የሁሉም ሰው አደጋ ተመሳሳይ አይደለም። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የማህበረሰቡ ዓባላት እና የጥቁር ማህበረሰቦች በከፍተኛ ሙቀት የተነሳ በንጽጽር በከፍተኛ ደረጃ ተጎጂ ናቸው፣ እና እነዚህ የአካባባቢ ሙቀት መከታተያዎች አሁን እና ለወደፊቱ ተጋላጭ የሆኑ የመኖሪያ ስፍራዎችን ለመከላከል እርምጃ የት መውሰድ እንዳለብን ያሳውቁናል።

የከተማ የሙቀት ደሴት መከታተያ መጠቆሚያዎች ላይ የበጎፈቃደኛ ምዝገባ

ሙቀቱ የት ይሰማዎታል?

በእርስዎ አስተያየት ሙቀትን በተመለከተ የትኛው የማህበረሰብ ቦታዎች ለምሳሌ ልክ እንደ ፓርኮች፣ የአውቶብስ ማቆሚያ ቦታዎች እና ትምህርት ቤቶች ወዘተ ይበልጥ አንገብጋቢ ናቸው ብለው ያስባሉ? በካውንቲው ውስጥ ከፍተኛ የሙቀት ልዩነት እንዳለባቸው የተመለከቷቸው አንዳንድ ቦታዎች፣ ለምሳሌ የመኪና ማቆሚያዎች ወይም መንገዶች የመሰሳሉት የትኛዎቹ ናቸው? ከታች የሚገኘው የሙቀት ካርታ ላይ ምልክት ያድርጉባቸው?

በካርታው ላይ የእርስዎን የቦታ መጠቆሚያ ለማከል ከታች ያለው ካርታ ላይ የመደመር ምልክትን ይጫኑ። ነባሩን ምልክት የተደረገበት ቦታ ላይ ይጫኑ እና ስጋት ያለበት ቦታ መሆኑን ለማመላከት “አውራ ጣት ወደላይ” አዝራርን ይጫኑ። በስም (ለምሳሌ፣ ቢል ኤለመንታሪ ስኩል) ቦታዎችን ማከል ይችላሉ ወይም ያልተሰየመ የመኪና ማቆሚያ ቦታ፣ የአውቶብስ ማቆሚያ፣ ወይም መገናኛ ቦታን በካርታው ላይ ለማሳየት የምልክት ማድረጊያውን ይጎትቱ።

Made with Padlet

 

የመንገድ ሳይንቲስት ይሁኑ፦

  • ሞንትጎመሪ ካውንቲ በመጪው የበጋ ከፍተኝ መቀት ወቅት ስለ ክልላችን በጣም ምቃታማ እና ቀዝቃዛ ቦታዎች መረጃ የሚሰበስቡ የበጎፈቃድ የመንገድ ሳይንቲስቶችን ለመመልመል ይፈልጋል።
  • በአንድ ቀን ውስጥ በሚጠናቀቀው የሙቀት መከታተል ዘመቻ ላይ፣ በበጎፈቃደኞች የሚሰበሰበው መረጃ የክልሉን የሙቀት እና የሙቀት ግለት ማውጪያ ካርታዎችን ለማዘጋጀት (ለምሳሌ ሲያትልን ይመልከቱ) እና በመላው ክልል ውስጥ የሚገኙ የሙቀት ተጋላጭነት ጋር የሚያያዙ ችግሮችን ለመፍታት ያገለግላሉ።
  • ኦገስት ላይ በተመደበ ቀን ላይ፣ በእርስዎ መኖሪያ አቅራቢያ ላይ እንደ አሽከርካሪ ሹፌር ወይም
  • ዳሳሽ በሶስት የአንድ ሰዓት ክፍለ ጊዜዎች ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የሙቀት እና የወበቅ ልኬቶችን መረጃ ይሰበስባሉ
  • የተሳታፊዎች የኪስ ገንዘብ እና ክፍያ የሚመለከት መረጃ ከበጎፈቃደኞች ጋር ለወደፊቱ ውይይት ይደረግበታል።

የመንገድ ላይ ሳይንቲስቶች የሚያደርጉት ምንድን ነው?

ሙቀት በሚጨምርበት ቀን ጠዋት፣ ከሰዓት በኋላ እና ምሽት ላይ ሦስት የተነጣጠሉ የአንድ ሰዓት ክፍለ ጊዜዎች ላይ በእርስዎ አከባቢ በቅድሚያ በታቀዱ መንገዶች ላይ የሚያሽከርክሩ የበጎፈቃድ ሰዎች ይፈለጋሉ። የበጎፈቃድ አሽከርካሪዎቹ በአካባቢው ውስጥ ያለውን ሙቀት እና ወበቅ ለመለካት በመኪናቸው ላይ የሚገጠሙ ቀላል የመረጃ መስብሰቢያ መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ። ልክ እንደ ቀያሽ በበጎፈቃደኝነት በመሳተፍ ለአሽከርካሪዎች በመንገዶቻቸው ላይ አቅጣጭ መስጠት ይችላሉ። 

የበጎፈቃደኛ ለመሆን ምን ያስፈልጋል?

አሽከርካሪ፣ ቀያሽ እና የመኖሪያ ስፍራ አደራጅ ጨምሮ ብዙ ዓይነት ሚናዎች በፕሮጀክቱ ውስጥ ስለሚኖሩ ማንኛውም ሰው እገዛ ለመስጠት መመዝገብ ይችላል። የመኪና አሽከርካሪዎች ሕጋዊ መንጃ ፈቃድ፣ የመኪና ኢንሹራንስ፣ እና መኪና በራሳቸው ማግኘት ይኖርባቸዋል።

የመኖሪያ ስፍራ አደራጅ ሚናዎች ምንድን ናቸው?

የመኖሪያ ስፍራ አደራጅ የበጎፈቃድ ሰራተኛ በሙቀት መከታተያ መጠቆሚያ ፕሮጀክቱን ንቁ ተሳታፊ የሆኑትን ማህበረሰቦች ስለ ፕሮጀክቱ እንዲረዱ እና እንዲሳተፉበት የሚያደርግ ግለሰብ ነው። ሚናው ተለዋዋጭ ነው እና ሹፌር ለመሆን የማይችሉ ከሆነ ወይም በፕሮጀክቱ ላይ በጥልቅ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ከሆነ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

የሙቀት መከታተያ መጠቆሚያ ዘመቻ በየትኛው ቀን ላይ ይከሰታል?

ይሄ እንደ የአየርንብረቱ ትንበያ ላይ ይወሰናል። የሙቀት መከታተያ መጠቆሚያ በጣም ሞቃታማ አየር እና የጠራ የቀን ሰማይ ያለው ቀን ላይ በተሻለ ሁኔታ ይሰራሉ። ያለፈውን የአየርንብረት ለውጥ ሂደት እና ከብሔራዊ የአየርንብረት አገልግሎት የሚገኘውን ድጋፍ በመጠቀም፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የታለሙት የዘመቻ ቀኖች የኦገስት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንቶች ናቸው። ምንም እንኳን አየርንብረቱ ቢቀያየርም፣ አየርንብረት ትንበያዎቹ ይበልጥ አስተማማኝ የሚሆኑበት ጥቂት ሳምንታት በፊት የዘመቻ ቀኑን ያረጋግጣል።

ምዝገባ

እባክዎ መመዝገብ ፕሮጀክቱ ላይ የግድ እንዲሳተፉ አያደርጎትም፣ ከዚያ ይልቅ፣ ሂደቱ የሚጀምረው ብቁ የሚሆኑ በጎፈቃደኞችን መለየት እና የእርስዎን ተሳታፊነት ለመለየት እናገኞታለን።



One comment on "በዚህ የበጋ ወቅት ላይ የማህበረሰብ የሙቀት መከታተያ መጠቆሚያ (heat mapping) ፕሮጀክት ላይ ይሳተፉ!"

  1. Alemayehu Jemaneh says:

    I am very eagre and happy to participate in this kind of project/program. Thank you for your initiation.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *